All tagged Amharic Christian Blog

ሰላምና ደስታ

ዛሬ ገና ከእንቅልፌ ስነቃ ነው ውስጤ በደስታ የተሞላው። ፈገግ እያልኩኝ ነው ከአልጋዬ የወረድኩት ነው የምላችሁ። እኔ መሳቅና መደሰትን ከእግዚአብሄር እንደ ተሰጡኝ በረከቶች ነው የምቆጥራቸው። እውነተኛ የልብ ደስታ የሚመጣው ከእግዚአብሄር ዘንድ ብቻ እንደሆነ ልቤ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ተምሯል።

ምርጫ 

መቼም ህይወታችን የየቀን ምርጫዎቻችን ውጤት መሆኑን ብዙዎቻችን እናስተውላለን። አብዛኞቹ ህይወታችን ላይ ያሉት ነገሮች፥ የእኛ ምርጫ ውጤቶች ናቸው። ለምሳሌ የምንሰራበትን መስሪያ ቤት መርጠን ማመልከቻ አስገብተን ነው የገባነው።

መወደድ 

በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር።

ፍለጋ

የዘጸአትን መጽሀፍ ሳነብ፥ አንድ እስከዛሬ ያላስተዋልኩትን ነገር አነበብኩ። በመጽሀፉ 33ተኛ ምእራፍ ላይ እንደሚናገረው፥ ሙሴ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበትን የመገናኛ ድንኳን የተከለው፥ ሰፈር ውስጥ አልነበረም። የተከለው ከሰፈር ውጪ፣ ከመንደር ውጪ፣ አብዛኛው ሰው ከሚኖርበት ሰፈር ውጪ ነበር።

 ዝግጅት

ዛሬ ረፈድፈድ አርጌ ነው ከመኝታዬ የተነሳሁት። ተነስቼ ልቤ ወደ ቀኑ ጉዳዮቼ ቢቸኩልም፥ ህረ በሰላም ያሳደረኝን ተመስገን ልበለው። እግዚአብሄር ከረዳኝ ደግሞ ከቅዱስ ቃሉ ለቀኔ የሚሆነኝን ጥቂት ነገር ላንብብ ብዬ የጀመርኩትን የማቴዎስ ወንጌል ማንበቤን ቀጠልኩ።

ያእቆብ

ሰሞኑን የህይወት ታሪኩን በማሰላሰል ልቤን በጣም የገዛው አንድ ሰው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አለ። ያእቆብ። መቼም ታሪኩን ምንም የማናውቀው ብንሆን እንኳን፥ ወይ በሰዎች ንግግር ውስጥ፥ ወይንም ደግሞ በህብረት ጸሎቶቻችን ውስጥ፥ የአብርሀም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ ተብሎ ሲጸለይ እንሰማለን።

ምስጋና 

በህይወቴ ላይ በተለያዩ ስሜቶች ውስጥ ያለፍኩባቸው የተለያዩ ቀናቶች አሉ። በጣም ደስተኛ የሆንኩባቸው፥ እግዚአብሄር ግን እንዴት መልካም አምላክ ነው ያልኩባቸው፣ የዘመርኩባቸውና እግዚአብሄርን የባረኩባቸው ብዙ ቀናቶች ህይወቴ ላይ አሉ። ልክ እንደዚሁ ደግሞ፥ በጣም ያዘንኩባቸው፥ ልቤ የተሰበረባቸው፣ እግዚአብሄርን ለምን ብዬ ለመጠየቅ የተነሳሁባቸውና ልቤ ከምስጋና እጅግ በጣም የራቀባቸው ቀናቶችም ህይወቴ ላይ ነበሩ።

ጥንቃቄ

ከህይወታቸው እንማረባቸው ዘንድ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ ከተጻፉልን ሰዎች መካከል ነው። ብዙ ጊዜም በየመድረኮቻችን ላይ ታሪኩ ለትምህርታችን ሲሰበክ እናውቀዋለን። ሳምሶን። የተቀባ በጣም ትልቅ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ሰው ነው።

መዳኔ

ዛሬ ከወትሮዬ ለየት ባለ መንገድ በክርስቶስ ውስጥ ስላገኘሁት የዘላለም መዳን ልቤ ሲገረምና ሲደነቅ ቆይቷል። አንዳንድ ቀን መዳኔ ልክ ስለሰራሁት መልካም ስራ የሚገባኝ ተመጣጣኝ ክፍያ ይመስል፣ በእግዚአብሄር ውስጥ እየኖርኩት ያለሁት ህይወት የማይገባኝና ከእግዚአብሄር ምህረት ብዛት የተሰጠኝ መሆኑን ልቤ ይዘነጋዋል:: በክርስቶስ ደም ተቀድሼ አንደበቴ ስለ ጽድቅ የማወራትን ድፍረት ማግኘቱን፣ የእግዚአብሄር ባሪያ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ልጅ ተብሎ የመጠራትን እድል ማግኘቴ ፈጽሞ የማይገባኝ ነገር መሆኑ ይረሳኛል።

ትምህርት ቤት

አንድ የቅርብ ጉዋደኛዬ በህክምና ፊልድ ውስጥ የመሆንና በዚህ የስራ ዘርፍ የማገልገል ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ስለነበራት፥ በነርሲንግ ፕሮግራም ውስጥ ገብታ ለሁለት አመታቶች በትጋት ትምህርትዋን ትከታተል ነበር። የቅርብ ወዳጄ በመሆንዋ፥ በተገናኘንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ የትምህርትዋን ሁኔታ ታጫውተኝ ነበር።

ችላ ያልነው ጠላታችን

አንዳንድ ጊዜ ስፀልይ፥ ስዘምር፥ መፅሀፍ ቅዱሴን ሳነብ በጣም መንፈሳዊ እንደሆንኩ ብቻ ሳይሆን መልአክ እንደሆንኩኝም ነው የሚሰማኝ። በግራና በቀኜ ያሉትን ክንፎቼን ፈልጌ ሳላበቃ፥ መልሼ ራሴን የማልጠብቀው ቦታ ላይ አገኘዋለሁ።

ልቤ

ዛሬ ቀኑ ፀሀያማና ደስ የሚል ነው። እኔም ከሰዎች ጋር አንድ አስፈላጊ ቀጠሮ ስላለኝ ወደዛ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው። መዘነጥ አይበላችሁ! ፏ ብያለሁ! የክት ልብሴን ለባብሼ፥ ፀጉሬን አስተካክዬ፥ ሽቶዬን ተቀባብቼ ከጨረስኩ በኋላ፥ ከመውጣቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ራሴን በመስታወት ማየት ስለነበረብኝ ወደ መስታወቱ ጋር ጠጋ ብዬ ራሴን ማየት ጀመርኩ። እዛው እንደቆምኩ ጥቂትም ሳይቆይ ነው ሀሳቦች በልቤ መምጣት የጀመሩት።

ደውል

አንዳንድ ጊዜ ቤቴ ውስጥ ቡና ሳፈላ፥ ጣሪያ ላይ ያለችው የእሳት አደጋ ደውል የቡናውን ጭስ ሰምታ ጩኸትዋን ታቀልጠዋለች። በሩን ከፍቼ የቡናውን ጭስ ካላስወጣሁትማ፥ እልህ ይይዛታል መሰለኝ ብሶባት ነው ቁጭ የሚለው። ለነገሩ እሷ ምን ታርግ? ስራዋን እኮ በአግባቡ እየሰራች ነው።

ሩጫ

በልጅነቴ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ሩጫ ነበር። በአጭሩ፥ ቆመን እናውራ ከምትሉኝ እየሮጥን እናውራ ብትሉኝ ይቀለኝ ነበር። አንዳንዴማ ማዘር ሱቅ ስትልከኝ፥ ለመሮጥ ከመቸኮሌ የተነሳ የምገዛውን ነገር በሙሉ ተናግራ እስክትጨርስ ለመስማት የሚሆን ትእግስት አልነበረኝም። እሷ ተናግራ ሳትጨርስ እኔ ሮጬ ሱቁ ጋር ደርሻለሁ። ግዢ ያለችኝን ነገሮች በትክክል ስላልሰማሁ ተመልሼ ስመጣ፥ ማዘር እዛው ቦታ ጋር ቆማ እየጠበቀችኝ ነው።

መታዘዝ

ዛሬ በጠዋት አስፈላጊ የሆነ ቀጠሮ ስለነበረኝ በጊዜ ነበር ለመሄድ የተነሳሁት። መሄድ የነበረብኝ ቦታ እኔ ከምኖርበት ሰፈር ራቅ ያለ ስለነበር፥ የቦታውን አድራሻ ወስጄ ስልኬን ወደዛ ቦታ እንድትመራኝ በትህትና ጠየኳት። እግዚአብሄር ይስጣት ለደቂቃ እንኳን ሳታንገራግር ነው እሺ ብላ የምፈልግበት ቦታ ያደረሰችኝ። ዝም ብዬ ግን አልደረስኩም። ወደምፈልገው ቦታ ለመድረስ የእሷን ምሪት ተማምኜ አርጊ ያለችኝን ሁሉ ነው ያደረኩት።

የተፈጠርኩበትን ዓላማ የማውቀው እንዴት ነው?

ብዙ ሰው በህይወቱ መጨረሻ ቁጭቶች ይኖሩታል። ይሄንን ነገር ማድረግ ነበረብኝ ወይንም ማድረግ አልነበረብኝም የሚላቸው ነገሮች ይበዛሉ። በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በእድሜው መጨረሻ ህይወቱን ዞር ብሎ አይቶ የእርካታና የደስታ ንግግር ከተናገሩ ሰዎች መካከል አንዱ ጳውሎስ ነው።

አላማ

አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጆችን ህይወት ቆም ብላችሁ ስታስቡት በተመሳሳይ ነገር የተሞላ ነው:: ሰው ይወለዳል, ያድጋል, ይማራል, ያገባል, ይወልዳል, ከቻለ ቤት እና መኪና ይገዛል, ከዚያ ያረጅና ይሞታል:: የሚያረጀውም እግዚእብሄር እድሜና ጤና ከሰጠው ብቻ ነው:: የሰው ልጅ ህይወቱ ከዚህ ተመሳሳይ ድግግሞሽ አያመልጥም:: እግዚአብሄር የጥበብን መንፈስ የሞላበት ሰው ጠቢቡ ሰለሞን ህይወትንና የሰው ልጆችን እንቅስቃሴ ሁሉ አስተውሎ ከተመለከተ በሗላ ያለው ነገር ይገርመኛል:: “... ከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው...”