All in Amharic blogs

ተዋጊ

ሰሞኑን እየተማርኩ ያለሁት ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ነው። “እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም ደግሞ እግዚአብሔር ነው” በማለት በዘጸአት 15፡3 ላይ እንደተጻፈው፥ የምናመልከው አምላክ ተዋጊ እንደሆነ ሁሉ እኛም ህዝቦቹ ተዋጊ ሰራዊቶች እንድንሆን ይፈልጋል። አንድ ጊዜ እንዲያውም በመሳፍንት መጽሐፍ ምእራፍ 3 ከቁጥር 1 ጀምሮ ስትመለከቱ፥ እግዚአብሔር ሆነ ብሎ የእስራኤል ልጆች መዋጋትን ይማሩ ዘንድ፥ ሰልፍን ይለማመዱ ዘንድ ሙሉ በሙሉ ጠላቶቻቸውን ሊያጠፋ እንዳልወደደና ጥቂት ጠላቶችን እንዳስቀረ በክፍሉ ላይ ይናገራል። እግዚአብሔር መዋጋትን እንድናውቅ፥ ሰልፍን እንድንማር ይፈልጋል።

ሰላምና ደስታ

ዛሬ ገና ከእንቅልፌ ስነቃ ነው ውስጤ በደስታ የተሞላው። ፈገግ እያልኩኝ ነው ከአልጋዬ የወረድኩት ነው የምላችሁ። እኔ መሳቅና መደሰትን ከእግዚአብሄር እንደ ተሰጡኝ በረከቶች ነው የምቆጥራቸው። እውነተኛ የልብ ደስታ የሚመጣው ከእግዚአብሄር ዘንድ ብቻ እንደሆነ ልቤ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ተምሯል።

ምርጫ 

መቼም ህይወታችን የየቀን ምርጫዎቻችን ውጤት መሆኑን ብዙዎቻችን እናስተውላለን። አብዛኞቹ ህይወታችን ላይ ያሉት ነገሮች፥ የእኛ ምርጫ ውጤቶች ናቸው። ለምሳሌ የምንሰራበትን መስሪያ ቤት መርጠን ማመልከቻ አስገብተን ነው የገባነው።

መወደድ 

በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር።

ፍለጋ

የዘጸአትን መጽሀፍ ሳነብ፥ አንድ እስከዛሬ ያላስተዋልኩትን ነገር አነበብኩ። በመጽሀፉ 33ተኛ ምእራፍ ላይ እንደሚናገረው፥ ሙሴ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበትን የመገናኛ ድንኳን የተከለው፥ ሰፈር ውስጥ አልነበረም። የተከለው ከሰፈር ውጪ፣ ከመንደር ውጪ፣ አብዛኛው ሰው ከሚኖርበት ሰፈር ውጪ ነበር።

 ዝግጅት

ዛሬ ረፈድፈድ አርጌ ነው ከመኝታዬ የተነሳሁት። ተነስቼ ልቤ ወደ ቀኑ ጉዳዮቼ ቢቸኩልም፥ ህረ በሰላም ያሳደረኝን ተመስገን ልበለው። እግዚአብሄር ከረዳኝ ደግሞ ከቅዱስ ቃሉ ለቀኔ የሚሆነኝን ጥቂት ነገር ላንብብ ብዬ የጀመርኩትን የማቴዎስ ወንጌል ማንበቤን ቀጠልኩ።

እውቀት

በምድር ላይ ሰዎችን የተሻለ እንዲሰሩ፣ በተሻለ መንገድ ነገሮችን እንዲያከናውኑ የሚረዳቸው ነገር ነው እውቀት። እኛ እንኳን በየቀን ኑሮአችን ውስጥ በምንፈልጋቸው የተለያዩ እርዳታዎች ዙሪያ የምንፈልገው እውቀት ያለውን ሰው ነው። ለምሳሌ ትንሽ ቢያመን፥ እኛን የሚረዳበት እውቀት ያለው የህክምና ባለሙያ ስለሆነ ቶሎ የምናስበው ወደ ዶክተራችን ጋር ለመሄድ ነው።

አንዲቷ  ልመና

ከሌሊቶች ውስጥ በአንዱ ሌሊት ነው እግዚአብሄር ለንጉስ ሰለሞን በራእይ ተገልጦ ምን እንድሰጥህ ለምነኝ ያለው። ለእኛ ለሰዎች መለመን ብዙም የሚያስደስተን ነገር አይደለም። ምክኒያቱ ደግሞ የበዛውን ጊዜ ለመስጠት ስንነሳ፥ ከራሳችን የሚጎልብን ነገር ስላለ ነው።

ጠቢብ

መጽሀፍ ቅዱሳችንን ስናጠና፥ በስፋትና በተደጋጋሚ እየተጠቀሰ የምናገኘው ነገር ነው ጥበብ። በተለይም የምሳሌ መጽሀፍ እየደጋገመ አየደጋገመ ያነሳዋል።

ያእቆብ

ሰሞኑን የህይወት ታሪኩን በማሰላሰል ልቤን በጣም የገዛው አንድ ሰው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አለ። ያእቆብ። መቼም ታሪኩን ምንም የማናውቀው ብንሆን እንኳን፥ ወይ በሰዎች ንግግር ውስጥ፥ ወይንም ደግሞ በህብረት ጸሎቶቻችን ውስጥ፥ የአብርሀም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ ተብሎ ሲጸለይ እንሰማለን።

ማንነት

እቤት ውስጥ ያደግነው፥ እኔ እና እህቴ ሆነን ነው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው ብለው እነደሚናገሩት፥ ይሄ ተረትና ምሳሌ ትክክለኛ ተፈጻሚነትን ያገኘው እኛ ቤት ይመስላል። እኔና እህቴ ልጆች እያለን፥ ትንሽ እንኳን ሊቀራረብና ሊመሳሰል የማይችል የባህሪ ልዩነት ነበር የነበረን። አንዳንድ ቀን እንተያይና እንዴት እህትማማቾች ልንሆን እንደቻልን ሁለታችንም እንገረማለን።

ምስጋና 

በህይወቴ ላይ በተለያዩ ስሜቶች ውስጥ ያለፍኩባቸው የተለያዩ ቀናቶች አሉ። በጣም ደስተኛ የሆንኩባቸው፥ እግዚአብሄር ግን እንዴት መልካም አምላክ ነው ያልኩባቸው፣ የዘመርኩባቸውና እግዚአብሄርን የባረኩባቸው ብዙ ቀናቶች ህይወቴ ላይ አሉ። ልክ እንደዚሁ ደግሞ፥ በጣም ያዘንኩባቸው፥ ልቤ የተሰበረባቸው፣ እግዚአብሄርን ለምን ብዬ ለመጠየቅ የተነሳሁባቸውና ልቤ ከምስጋና እጅግ በጣም የራቀባቸው ቀናቶችም ህይወቴ ላይ ነበሩ።

ይሉኝታ

ቃሉ ከህይወታችንና ከአካባቢያችን የራቀ አይደለም። ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ የይሉኝታ ስሜት ተሰምቶን ያውቃል። ሰው ስለእኛ የሚለው ነገር፥ ሰው ስለ እኛ የሚያስበው ነገር ያሳስበናል። ብዙ ጊዜ ማድረግ የምንፈልጋቸውን ነገሮች፥ ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን ፈርተን ሳናረጋቸው ቀርተን እናውቃለን። ማድረግ የማንፈልጋቸውን ነገሮች ደግሞ ሰው ምን ይለኛል ብለን ፈርተን አርገናቸው እናውቃለን። የእኛ ሀገር ባህል ደግሞ ጥሎበት ከይሉኝታ ጋር እጅግ በጣም የተሳሰረ ነው።

ጥንቃቄ

ከህይወታቸው እንማረባቸው ዘንድ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ ከተጻፉልን ሰዎች መካከል ነው። ብዙ ጊዜም በየመድረኮቻችን ላይ ታሪኩ ለትምህርታችን ሲሰበክ እናውቀዋለን። ሳምሶን። የተቀባ በጣም ትልቅ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ሰው ነው።

መዳኔ

ዛሬ ከወትሮዬ ለየት ባለ መንገድ በክርስቶስ ውስጥ ስላገኘሁት የዘላለም መዳን ልቤ ሲገረምና ሲደነቅ ቆይቷል። አንዳንድ ቀን መዳኔ ልክ ስለሰራሁት መልካም ስራ የሚገባኝ ተመጣጣኝ ክፍያ ይመስል፣ በእግዚአብሄር ውስጥ እየኖርኩት ያለሁት ህይወት የማይገባኝና ከእግዚአብሄር ምህረት ብዛት የተሰጠኝ መሆኑን ልቤ ይዘነጋዋል:: በክርስቶስ ደም ተቀድሼ አንደበቴ ስለ ጽድቅ የማወራትን ድፍረት ማግኘቱን፣ የእግዚአብሄር ባሪያ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ልጅ ተብሎ የመጠራትን እድል ማግኘቴ ፈጽሞ የማይገባኝ ነገር መሆኑ ይረሳኛል።

ሩት

ስራ በሌለኝና በእረፍት ቀናቶቼ ማድረግ ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ፣ በጠዋት ተነስቶ አሪፍ ውሀ ዳር ያለ ፓርክ በመሄድ፣ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ ማድረግ ነው። እንዴት አንደሚያዝናናኝ እንዴት ብዬ ልንገራችሁ! በተለይ በበጋና አየሩ ሞቃታማ በሆነባቸው ጊዜያቶች፣ የማለዳው ጸሀይ ነፋሻማ ከሆነው ተስማሚ አየርና በዙሪያዬ ከማያቸው የተለያዩ የተፈጥሮ ውጤቶች ጋር ተደምሮ፣ በደስታ ብዛት ሩጪ ሩጪ ስለሚለኝ ያሰብኩትን ቀላል የእግር ጉዞ ወደ ሩጫ እቀይረዋለሁ።

ስኬት

ስኬት ስለሚለው ቃል ስናስብ መቼም ሁላችንም ልብ ውስጥ የሚመጡ ይሄን ይሄን ባሳካ ብለን በልባችን ውስጥ የምናስባቸው፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስኬቶች ይኖሩናል። ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ በአካባቢያችን ላይ የምናውቃቸው ወይንም በsocial media ገጾቻችን እነሱ እንኳን ሳያውቁን እኛ የምናውቃቸውና የምንከተላቸው፣ በየቀኑ የሚያወጡትን ፎቶዎች እያየን የስኬት ምሳሌዎች ያረግናቸው ሰዎችም ይኖራሉ። ስኬት ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም ያለውና በህይወት ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች ጋር የተያያዘ ነገር ነው።

መማር

ሰሞኑን የኢያሱን መጽሀፍ በፍቅር ነው እያነበብኩት ያለሁት። መጽሀፉን በአንድ ቃል ግለጪው ተብዬ ብጠየቅ መውጣትና መውረስ ብዬ እገልጸዋለሁ። ለነገሩ ገና መጽሀፉስ ሲጀምር እግዚአብሄር ለኢያሱ መጥቶ ለአባቶቻቸው አሰጣችሀዋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ህዝብ ታወርሳለህና ጽና አይዞህ። ብሎ በእሱ ህይወት ሊሰራ ያሰበውን የማውረስ አገልግሎት አይደል እንዴ ቀድሞስ ቢሆን የተናገረው።

ኢዮብ

ብዙ ነገሮችን እንዳስብና እንዳሰላስል ከሚያደርጉኝ መፅሀፎች ውስጥ አንዱ የኢዮብ መፅሀፍ ነው። ብዙ ጊዜ የኢዮብን መፅሀፍ ስናስብ ቶሎ ብሎ ትዝ የሚለን፥ ኢዮብ ያለፈባቸው በጣም ከባባድ ፈተናዎች ናቸው። መቼም የእግዚአብሄር ፀጋ የማያሳልፈው ነገር የለም እንጂ ማናችንም ብንሆን፥ ኢዮብ ያለፈባቸውን ፈተናዎች እንኳን ልናልፍባቸው፥ ለማሰብ እንኳን የሚከብዱን ናቸው።