በማመልክበት ቤተክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ የሆነ አንድ ወንድም የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ላይ እያለ አንድ ጥያቄ ጉባኤውን ጠየቀ።
Welcome to my site! I hope and pray that the blogs I post encourages and uplifts you to keep building a deeper relationship with the Lord.
God bless you!
በማመልክበት ቤተክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ የሆነ አንድ ወንድም የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ላይ እያለ አንድ ጥያቄ ጉባኤውን ጠየቀ።
የነህምያን ታሪክ ሳጠና ከሕይወቱና ከአገልግሎቱ ከተማርኳቸው ጥቂት ነጥቦች ውስጥ፥ ለጥቂት ሰዎች የሚቀር ነገር ካለ ብዬ ለመጻፍና ለማካፈል ብእሬን አንስቻለሁ።
ሰሞኑን እየተማርኩ ያለሁት ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ነው። “እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም ደግሞ እግዚአብሔር ነው” በማለት በዘጸአት 15፡3 ላይ እንደተጻፈው፥ የምናመልከው አምላክ ተዋጊ እንደሆነ ሁሉ እኛም ህዝቦቹ ተዋጊ ሰራዊቶች እንድንሆን ይፈልጋል። አንድ ጊዜ እንዲያውም በመሳፍንት መጽሐፍ ምእራፍ 3 ከቁጥር 1 ጀምሮ ስትመለከቱ፥ እግዚአብሔር ሆነ ብሎ የእስራኤል ልጆች መዋጋትን ይማሩ ዘንድ፥ ሰልፍን ይለማመዱ ዘንድ ሙሉ በሙሉ ጠላቶቻቸውን ሊያጠፋ እንዳልወደደና ጥቂት ጠላቶችን እንዳስቀረ በክፍሉ ላይ ይናገራል። እግዚአብሔር መዋጋትን እንድናውቅ፥ ሰልፍን እንድንማር ይፈልጋል።
ዛሬ ገና ከእንቅልፌ ስነቃ ነው ውስጤ በደስታ የተሞላው። ፈገግ እያልኩኝ ነው ከአልጋዬ የወረድኩት ነው የምላችሁ። እኔ መሳቅና መደሰትን ከእግዚአብሄር እንደ ተሰጡኝ በረከቶች ነው የምቆጥራቸው። እውነተኛ የልብ ደስታ የሚመጣው ከእግዚአብሄር ዘንድ ብቻ እንደሆነ ልቤ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ተምሯል።
መቼም ህይወታችን የየቀን ምርጫዎቻችን ውጤት መሆኑን ብዙዎቻችን እናስተውላለን። አብዛኞቹ ህይወታችን ላይ ያሉት ነገሮች፥ የእኛ ምርጫ ውጤቶች ናቸው። ለምሳሌ የምንሰራበትን መስሪያ ቤት መርጠን ማመልከቻ አስገብተን ነው የገባነው።
በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር።
የዘጸአትን መጽሀፍ ሳነብ፥ አንድ እስከዛሬ ያላስተዋልኩትን ነገር አነበብኩ። በመጽሀፉ 33ተኛ ምእራፍ ላይ እንደሚናገረው፥ ሙሴ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበትን የመገናኛ ድንኳን የተከለው፥ ሰፈር ውስጥ አልነበረም። የተከለው ከሰፈር ውጪ፣ ከመንደር ውጪ፣ አብዛኛው ሰው ከሚኖርበት ሰፈር ውጪ ነበር።
ዛሬ ረፈድፈድ አርጌ ነው ከመኝታዬ የተነሳሁት። ተነስቼ ልቤ ወደ ቀኑ ጉዳዮቼ ቢቸኩልም፥ ህረ በሰላም ያሳደረኝን ተመስገን ልበለው። እግዚአብሄር ከረዳኝ ደግሞ ከቅዱስ ቃሉ ለቀኔ የሚሆነኝን ጥቂት ነገር ላንብብ ብዬ የጀመርኩትን የማቴዎስ ወንጌል ማንበቤን ቀጠልኩ።
በምድር ላይ ሰዎችን የተሻለ እንዲሰሩ፣ በተሻለ መንገድ ነገሮችን እንዲያከናውኑ የሚረዳቸው ነገር ነው እውቀት። እኛ እንኳን በየቀን ኑሮአችን ውስጥ በምንፈልጋቸው የተለያዩ እርዳታዎች ዙሪያ የምንፈልገው እውቀት ያለውን ሰው ነው። ለምሳሌ ትንሽ ቢያመን፥ እኛን የሚረዳበት እውቀት ያለው የህክምና ባለሙያ ስለሆነ ቶሎ የምናስበው ወደ ዶክተራችን ጋር ለመሄድ ነው።
ከሌሊቶች ውስጥ በአንዱ ሌሊት ነው እግዚአብሄር ለንጉስ ሰለሞን በራእይ ተገልጦ ምን እንድሰጥህ ለምነኝ ያለው። ለእኛ ለሰዎች መለመን ብዙም የሚያስደስተን ነገር አይደለም። ምክኒያቱ ደግሞ የበዛውን ጊዜ ለመስጠት ስንነሳ፥ ከራሳችን የሚጎልብን ነገር ስላለ ነው።
መጽሀፍ ቅዱሳችንን ስናጠና፥ በስፋትና በተደጋጋሚ እየተጠቀሰ የምናገኘው ነገር ነው ጥበብ። በተለይም የምሳሌ መጽሀፍ እየደጋገመ አየደጋገመ ያነሳዋል።
ሰሞኑን የህይወት ታሪኩን በማሰላሰል ልቤን በጣም የገዛው አንድ ሰው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አለ። ያእቆብ። መቼም ታሪኩን ምንም የማናውቀው ብንሆን እንኳን፥ ወይ በሰዎች ንግግር ውስጥ፥ ወይንም ደግሞ በህብረት ጸሎቶቻችን ውስጥ፥ የአብርሀም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ ተብሎ ሲጸለይ እንሰማለን።
እቤት ውስጥ ያደግነው፥ እኔ እና እህቴ ሆነን ነው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው ብለው እነደሚናገሩት፥ ይሄ ተረትና ምሳሌ ትክክለኛ ተፈጻሚነትን ያገኘው እኛ ቤት ይመስላል። እኔና እህቴ ልጆች እያለን፥ ትንሽ እንኳን ሊቀራረብና ሊመሳሰል የማይችል የባህሪ ልዩነት ነበር የነበረን። አንዳንድ ቀን እንተያይና እንዴት እህትማማቾች ልንሆን እንደቻልን ሁለታችንም እንገረማለን።
በህይወቴ ላይ በተለያዩ ስሜቶች ውስጥ ያለፍኩባቸው የተለያዩ ቀናቶች አሉ። በጣም ደስተኛ የሆንኩባቸው፥ እግዚአብሄር ግን እንዴት መልካም አምላክ ነው ያልኩባቸው፣ የዘመርኩባቸውና እግዚአብሄርን የባረኩባቸው ብዙ ቀናቶች ህይወቴ ላይ አሉ። ልክ እንደዚሁ ደግሞ፥ በጣም ያዘንኩባቸው፥ ልቤ የተሰበረባቸው፣ እግዚአብሄርን ለምን ብዬ ለመጠየቅ የተነሳሁባቸውና ልቤ ከምስጋና እጅግ በጣም የራቀባቸው ቀናቶችም ህይወቴ ላይ ነበሩ።
ቃሉ ከህይወታችንና ከአካባቢያችን የራቀ አይደለም። ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ የይሉኝታ ስሜት ተሰምቶን ያውቃል። ሰው ስለእኛ የሚለው ነገር፥ ሰው ስለ እኛ የሚያስበው ነገር ያሳስበናል። ብዙ ጊዜ ማድረግ የምንፈልጋቸውን ነገሮች፥ ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን ፈርተን ሳናረጋቸው ቀርተን እናውቃለን። ማድረግ የማንፈልጋቸውን ነገሮች ደግሞ ሰው ምን ይለኛል ብለን ፈርተን አርገናቸው እናውቃለን። የእኛ ሀገር ባህል ደግሞ ጥሎበት ከይሉኝታ ጋር እጅግ በጣም የተሳሰረ ነው።
ብቻዬን ሆኜ ጊዜ ለማሳለፍ እድል በማገኝባቸው ጊዜያቶች ደስ ከሚለኝ ነገሮች አንዱ ወደ ኋላ ሄጄ ያለፈውን ታሪኬን ማሰብ ነው። ማሰብ ደስ ይለኛል። ዝም ብሎ ማሰብ። ገና ከመወለዴ ጀምሮ እናቴ ስለእኔ ከነገረችኝ ታሪኮች አንስቼ ልጅነቴን እንዲሁም ህይወቴ ያለፈባቸውን መንገዶች በሙሉ ቁጭ ብዬ አስባቸዋለሁ።
ከህይወታቸው እንማረባቸው ዘንድ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ ከተጻፉልን ሰዎች መካከል ነው። ብዙ ጊዜም በየመድረኮቻችን ላይ ታሪኩ ለትምህርታችን ሲሰበክ እናውቀዋለን። ሳምሶን። የተቀባ በጣም ትልቅ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ሰው ነው።
ዛሬ ከወትሮዬ ለየት ባለ መንገድ በክርስቶስ ውስጥ ስላገኘሁት የዘላለም መዳን ልቤ ሲገረምና ሲደነቅ ቆይቷል። አንዳንድ ቀን መዳኔ ልክ ስለሰራሁት መልካም ስራ የሚገባኝ ተመጣጣኝ ክፍያ ይመስል፣ በእግዚአብሄር ውስጥ እየኖርኩት ያለሁት ህይወት የማይገባኝና ከእግዚአብሄር ምህረት ብዛት የተሰጠኝ መሆኑን ልቤ ይዘነጋዋል:: በክርስቶስ ደም ተቀድሼ አንደበቴ ስለ ጽድቅ የማወራትን ድፍረት ማግኘቱን፣ የእግዚአብሄር ባሪያ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ልጅ ተብሎ የመጠራትን እድል ማግኘቴ ፈጽሞ የማይገባኝ ነገር መሆኑ ይረሳኛል።
ስራ በሌለኝና በእረፍት ቀናቶቼ ማድረግ ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ፣ በጠዋት ተነስቶ አሪፍ ውሀ ዳር ያለ ፓርክ በመሄድ፣ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ ማድረግ ነው። እንዴት አንደሚያዝናናኝ እንዴት ብዬ ልንገራችሁ! በተለይ በበጋና አየሩ ሞቃታማ በሆነባቸው ጊዜያቶች፣ የማለዳው ጸሀይ ነፋሻማ ከሆነው ተስማሚ አየርና በዙሪያዬ ከማያቸው የተለያዩ የተፈጥሮ ውጤቶች ጋር ተደምሮ፣ በደስታ ብዛት ሩጪ ሩጪ ስለሚለኝ ያሰብኩትን ቀላል የእግር ጉዞ ወደ ሩጫ እቀይረዋለሁ።