All in Amharic blogs

ትምህርት ቤት

አንድ የቅርብ ጉዋደኛዬ በህክምና ፊልድ ውስጥ የመሆንና በዚህ የስራ ዘርፍ የማገልገል ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ስለነበራት፥ በነርሲንግ ፕሮግራም ውስጥ ገብታ ለሁለት አመታቶች በትጋት ትምህርትዋን ትከታተል ነበር። የቅርብ ወዳጄ በመሆንዋ፥ በተገናኘንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ የትምህርትዋን ሁኔታ ታጫውተኝ ነበር።

ችላ ያልነው ጠላታችን

አንዳንድ ጊዜ ስፀልይ፥ ስዘምር፥ መፅሀፍ ቅዱሴን ሳነብ በጣም መንፈሳዊ እንደሆንኩ ብቻ ሳይሆን መልአክ እንደሆንኩኝም ነው የሚሰማኝ። በግራና በቀኜ ያሉትን ክንፎቼን ፈልጌ ሳላበቃ፥ መልሼ ራሴን የማልጠብቀው ቦታ ላይ አገኘዋለሁ።

ልቤ

ዛሬ ቀኑ ፀሀያማና ደስ የሚል ነው። እኔም ከሰዎች ጋር አንድ አስፈላጊ ቀጠሮ ስላለኝ ወደዛ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው። መዘነጥ አይበላችሁ! ፏ ብያለሁ! የክት ልብሴን ለባብሼ፥ ፀጉሬን አስተካክዬ፥ ሽቶዬን ተቀባብቼ ከጨረስኩ በኋላ፥ ከመውጣቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ራሴን በመስታወት ማየት ስለነበረብኝ ወደ መስታወቱ ጋር ጠጋ ብዬ ራሴን ማየት ጀመርኩ። እዛው እንደቆምኩ ጥቂትም ሳይቆይ ነው ሀሳቦች በልቤ መምጣት የጀመሩት።

ደውል

አንዳንድ ጊዜ ቤቴ ውስጥ ቡና ሳፈላ፥ ጣሪያ ላይ ያለችው የእሳት አደጋ ደውል የቡናውን ጭስ ሰምታ ጩኸትዋን ታቀልጠዋለች። በሩን ከፍቼ የቡናውን ጭስ ካላስወጣሁትማ፥ እልህ ይይዛታል መሰለኝ ብሶባት ነው ቁጭ የሚለው። ለነገሩ እሷ ምን ታርግ? ስራዋን እኮ በአግባቡ እየሰራች ነው።

ሩጫ

በልጅነቴ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ሩጫ ነበር። በአጭሩ፥ ቆመን እናውራ ከምትሉኝ እየሮጥን እናውራ ብትሉኝ ይቀለኝ ነበር። አንዳንዴማ ማዘር ሱቅ ስትልከኝ፥ ለመሮጥ ከመቸኮሌ የተነሳ የምገዛውን ነገር በሙሉ ተናግራ እስክትጨርስ ለመስማት የሚሆን ትእግስት አልነበረኝም። እሷ ተናግራ ሳትጨርስ እኔ ሮጬ ሱቁ ጋር ደርሻለሁ። ግዢ ያለችኝን ነገሮች በትክክል ስላልሰማሁ ተመልሼ ስመጣ፥ ማዘር እዛው ቦታ ጋር ቆማ እየጠበቀችኝ ነው።

መታዘዝ

ዛሬ በጠዋት አስፈላጊ የሆነ ቀጠሮ ስለነበረኝ በጊዜ ነበር ለመሄድ የተነሳሁት። መሄድ የነበረብኝ ቦታ እኔ ከምኖርበት ሰፈር ራቅ ያለ ስለነበር፥ የቦታውን አድራሻ ወስጄ ስልኬን ወደዛ ቦታ እንድትመራኝ በትህትና ጠየኳት። እግዚአብሄር ይስጣት ለደቂቃ እንኳን ሳታንገራግር ነው እሺ ብላ የምፈልግበት ቦታ ያደረሰችኝ። ዝም ብዬ ግን አልደረስኩም። ወደምፈልገው ቦታ ለመድረስ የእሷን ምሪት ተማምኜ አርጊ ያለችኝን ሁሉ ነው ያደረኩት።

የተፈጠርኩበትን ዓላማ የማውቀው እንዴት ነው?

ብዙ ሰው በህይወቱ መጨረሻ ቁጭቶች ይኖሩታል። ይሄንን ነገር ማድረግ ነበረብኝ ወይንም ማድረግ አልነበረብኝም የሚላቸው ነገሮች ይበዛሉ። በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በእድሜው መጨረሻ ህይወቱን ዞር ብሎ አይቶ የእርካታና የደስታ ንግግር ከተናገሩ ሰዎች መካከል አንዱ ጳውሎስ ነው።

አላማ

አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጆችን ህይወት ቆም ብላችሁ ስታስቡት በተመሳሳይ ነገር የተሞላ ነው:: ሰው ይወለዳል, ያድጋል, ይማራል, ያገባል, ይወልዳል, ከቻለ ቤት እና መኪና ይገዛል, ከዚያ ያረጅና ይሞታል:: የሚያረጀውም እግዚእብሄር እድሜና ጤና ከሰጠው ብቻ ነው:: የሰው ልጅ ህይወቱ ከዚህ ተመሳሳይ ድግግሞሽ አያመልጥም:: እግዚአብሄር የጥበብን መንፈስ የሞላበት ሰው ጠቢቡ ሰለሞን ህይወትንና የሰው ልጆችን እንቅስቃሴ ሁሉ አስተውሎ ከተመለከተ በሗላ ያለው ነገር ይገርመኛል:: “... ከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው...”