All tagged Marriage prep

ከትዳር በፊት ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች

ዛሬ በጣም ደክሞኛል። ምን የመሰለ ሰርግ ላይ ውዬ አሁን ቅርብ ጊዜ ነው ወደ ቤቴ የገባሁት። አቤት ሙሽሮቹ እንዴት እንደሚያምሩ! ሚዜዎቹስ ብትሉ፥ የተነገረው የእግዚአብሄር ቃል፥ የቃልኪዳን ስነስርዓቱ፣ የሰርጉ አዳራሽ ደግሞ ማማሩ! አምልኮውንማ አጠይቁኝ፥ በቃ ቀውጢ ነበር። እስኪያልበን ድረስ መዝለላችን፥ አምልኮ የሚለውን ቃል ባይተካውም፥ ያው እየዘለልን ዘምረናል። ምናለበት ግን የእሁድ እሁድ የቤተክርስቲያን አምልኮአችንም እንዲህ ቢመስል! ማለት፥ ተፈቶ ሲያመልክ አይተነው የማናውቀው ሰው ሁሉ ሰርግ ላይ ሲፈታ እናየዋለን።