All tagged God sees the heart

ልቤ

ዛሬ ቀኑ ፀሀያማና ደስ የሚል ነው። እኔም ከሰዎች ጋር አንድ አስፈላጊ ቀጠሮ ስላለኝ ወደዛ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው። መዘነጥ አይበላችሁ! ፏ ብያለሁ! የክት ልብሴን ለባብሼ፥ ፀጉሬን አስተካክዬ፥ ሽቶዬን ተቀባብቼ ከጨረስኩ በኋላ፥ ከመውጣቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ራሴን በመስታወት ማየት ስለነበረብኝ ወደ መስታወቱ ጋር ጠጋ ብዬ ራሴን ማየት ጀመርኩ። እዛው እንደቆምኩ ጥቂትም ሳይቆይ ነው ሀሳቦች በልቤ መምጣት የጀመሩት።