All tagged Eternal perspectives

ዘላለም

ዛሬ ስራ ቦታዬ በስራ ብዛት የተጨናነቀ ነበር። የስራዬ ባህሪ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚያገናኘኝና ከሰዎች ጋር እንዳወራና እንድጫወት እድል የሚሰጠኝ ነው። በተፈጥሮዬ ከሰዎች ጋር መግባባት ለኔ ከባድ የሚባል ስራ ስላልሆነ፣ ስራዬን እወደዋለሁ። በስራዬ መካከል በምወስዳቸው የእረፍት ሰአቶች ግን የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። ጸጥታ።